Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል Asphalt wearing course በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል ከታች የተጠቀሰውን Asphat wearing course በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ/ቁ
|
የሚገዛው ዕቃ አይነት
|
መለኪያ
|
ብዛት
|
ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ
|
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት
|
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር
|
1 |
Asphalt wearing course,
|
በቶን
|
50,000
|
60 ቀን
|
ዻጉሜ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋቱ 4፡30
|
ጳጉሜ 04 2017 ዓ.ም ጠዋቱ 4:45
|
500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/
|
ስለዚህ:
1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገፅ WWW.PPA.gov.et ) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፣ እንዲሁም ተጨማሪ ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ ከላይ እስከተጠቀሰበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራጮች አስፋልት ማምረቻ ማሽኑ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ህጋዊ ውክልና ወይም በአማራጭነት ሌሎች ባለቤትነቱን ሊገልጹ የሚችሉ ህጋዊ ሰነዶች እንዲሁም በህግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ የአስፋልት ሚክስ ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፈቃድ ካለው ግለሰብ /ማህበር የተሰጠ ህጋዊ (በፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት የተረጋገጠ) የውክልና ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ማስያዣ (CPO)ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸው መሰረት ሲሆን ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ በባለስልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ 104 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ተራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
ስልክ ቁጥር፡-011-372-2815/ 011 371-4103
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን