Your cart is currently empty!
የአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት የተለያዩ እቃዎች እና የጥገና ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ት/ቤቱ መግዛት እና ማስጠገን ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የመጀመሪያ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር አፍ/ህ/ቁ.2/አጸ/ህጻ/የመ/ደ/ት/ቤት/01/2018 ዓ.ም
የአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት የተለያዩ በሎት ምድብ የተከፋፈሉ አጠቃላይ እቃዎች እና የጥገና ስራዎች ማለትም
- ሎት 1 የደንብ (የስራ ልብስ)
- ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3. የህትመት
- ሎት 4. አላቂ የህክምና እቃዎች
- ሎት 5. አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት 6. አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት 7. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት 8. ለፕላንት ማሽነሪ መሳሪያዎች መግዣ
- ሎት 9. ለህንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ እቃዎችና
- ሎት 10. የተለያዩ ለፕላንት ማሽነሪ ጥገና እንዲሁም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ት/ቤቱ መግዛት እና ማስጠገን ይፈልጋል።
ስለሆነም ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል።
1. በዘርፉ የተሰማሩና ጊዜው ያላለፈበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዘጋቢ ስለመሆናቸው እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ሰነዶችን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ከላይ በሎት ምድብ የተጠቀሱትን እቃዎች ዝርዝር የተካተተበት የግዥ የግልጽ ጨረታ መመሪያን የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በት/ቤት ውስጥ በሚገኘው የካሸር ቢሮ ቁጥር 4 በመግዛት መውሰድ ይችላሉ ። እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃችሁ አካል የምታመጡት ደበብዳቤ በምን ዘርፍ እንደተደራጃችሁ የሚገልጽ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባችኋል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚወዳደሩበትን የእቃዎች ማለትም
- ለሎት 1. 10000 ብር
- ለሎት 2. 15000 ብር
- ለሎት 3 3000 ብር
- ለሎት 4. 5000 ብር
- ለሎት 5. 7000 ብር
- ለሎት 6. 20000 ብር
- ሎት 7. 6000 ብር
- ሎት 8. 5000 ብር
- ሎት 9. 6000 ብር
- ሎት 10. 10000 ብር በት/ቤቱ ስም ከታወቀ ባንክ የተዘጋጀ ሲፒኦ በማስያዝ ማረጋገጫውን ከሚወዳደሩበት ሰነዶች ጋር ማስገባት ይኖርባችኋል።
5. እንዲሁም የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ለውል ማስከበሪያ የጠቅላላው የሚያሸናፉትን ዋጋ የሚሆን 10% ውል ሲዋዋሉ ማስያዝ ይኖርባችኋል።
6. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስፈልጉ ሰነዶች እና የእቃዎችን ዝርዝር ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ውስጥ በክፍል 4 ውስጥ በሚገኘው የዋጋ መሙያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን አጠቃላይ ሰነዶች ላይ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት የድርጅታችሁን ክብ ማህተም በማድረግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባችኋል።
7. ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችሉም።
8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሁሉም እቃዎች የቅርብ ጊዜ ምርት (ጊዜው ያላለፈበት ምርት) ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል። እንዲሁም ናሙና ለማቅረብ የሚቸገሩባቸውን እቃዎች በፎቶ የተደገፈ ጥራት ያለ ምስል ያለው ፎቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል።
9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛ የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከሆነ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 5፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በት/ቤት ውስጥ በሚገኘው የግዥ ክፍል ውስጥ ይከፈታል።
10. ት/ቤቱ የተሻላ የግዥ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ የት/ቤቱ አድራሻችን፡- አበበች ጎበና ህጻናት መርጃ አጠገብ ወይም ዮሐንስ ቤ/ክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው አቤት ሆስፒታል ሲደርሱ ወደ ውስጥ በሚየስገባው ኮብል ስቶን ገባ ብሎ ነው። ለበለጠ መረጃ የት/ቤቱ
ስልክ ቁጥር (011-1-57-25-91) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ት/ቤቱ
የአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት