በልደታ ክፍል ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የግብዓት ግዥ እና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Lessan(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቅያ

በልደታ ክፍል ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የግብዓት ግዥ እና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መሳተፍ ይችላሉ።

የሎት ምድብ       የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ

  1. የደንብ ልብስ ግዥ 20000
  2. የጽህፈት መሳርያ 20000
  3. የጽዳት መጠበቅያ እቃዎች 25000
  4. የጽዳት እቃዎች 10000
  5. የጥገና አገልግሎት ግዥ 2000
  6. የኤሌክትሮኒክስ ግዥ 15000

ተጫራቾች ሕጋዊ ለ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።

ተጫራቾች የዘመኑን የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

ተጫራቾች TIN number ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

ተጫራቾች ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የTOT/VAT ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቢ.ቁ 09 በመምጣት መዉሰድ ይችላሉ።

ከሎት 1-6 ላሉት ከጨረታ ሰነድ ጋር CPO ማቅረብ አለባቸዉ።

 ተጫራቾች ለዉል ማስከበርያ ላሸነፉት የእቃዉን ዋጋ ከ0.5% አስከ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸዉ የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10ኛው የሥራ ቀን በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛዉ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ) ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 09 ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ለሚጫረቱት ሎት CPO ማስያዝ እንጂ ቼክ እና ቢድ ቦንድ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳዉቃለን።

ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራች ድርጅቶች ለእቃ ማጓጓዣ የትራንስፖርት አገልግሎት በራሳቸዉ ወጪ መሸፈን ይጠበቅባቸዋል።

ተጫራች ድርጅቶች ለሚጫረቱት ግብዓት የጨረታ ሰነድ ከነሳምፕሉ ማቅረብ አለባቸዉ ዕለቱ በበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
አድራሻ፡- ጎላ ፓርክ ፊት ለፊት ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 011-554-1638
የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት