Your cart is currently empty!
በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግዥ መለያ ቁጥር 0007/2018
በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት እቃዎችን እና አገልግሎሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለዚህም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋስትና የባንክ ዋስትና ሲፒኦ /CPO ማስያዣ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ሎት 1 6211 የደንብ ልብስ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000
- ሎት 2 6212 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7000
- ሎት 3 6218 ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች የጨረታ ማከበሪያ ብር 7500
- ሎት 4 6214 መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች የጨረታ ማከበሪያ 60,000
- ሎት 5 6219 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1000
- ሎት 6 6213 ለህትመት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 12000
- ሎት 7 6313 ለፕላት ማሽነሪና ለመሳሪያ መግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8500
- ሎት 8 6314 ለህንፃ ለቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዥ የጨረታማስከበሪያ ብር 18000
- ሎት 9. 6243 ለፕላት ማሽነሪና ለመሳሪያ ዕድሳት እና ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000
- ሎት 10 6244 ለህንፃ፤ ለቁሳቁስ፤ ተገጣጣሚዎች ዕድሳት እና ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000
- ሎት 11 6233 የመስተንግዶ መሙያ ቅፅ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 13000
በዚህም መሰረት
1. በጨረታ ው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ድብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ማቅረብ ላለባቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በመንግስት ግ/ን/አስ/ ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢያዎ ምዝገባ አማራች ያላቸው አምራች የሆናችሁ ብቻ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /የጨረታ ዋስትና የባንክ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3 ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን እለት አንሰቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በተ/ሃ/ማኖት ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ/በፖስታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት በተ/ሃማኖት ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል። ነገር ግን በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻለው በአስረኛ ቀን እስከ አስራ አንድ ስዓት ተኩል 11፡30 ድረስ ብቻ ነው ። ከአስራ አንድ ሰዓት ተኩል በኃላ ማስገባት አይቻልም። አስራ አንደኛ /11ኛ/ ቀን ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል /3፡30 የሚከፈት ይሆናል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊትለ ሎት1፤ ሎት2፤ ሎት3፤ ሎት5፣ ሎት፤7 ሎት፡8 እናሎትዘ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ሎት፡ 6 እና ሎት፡ 4 መስሪያ ቤቱ ናሙና የሚያሳይ እና የሚሰጥ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎችና አገልግሎቶች ለእያንዳዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
7.የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ስርዝ ድልዝ ያለው ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎችና አገልግሎቶች በራሳቸው ትራንስፖርት ጤና ጣቢያችን ድረስ ማቅረብ ይኖርባችዋል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ ስልክ ቁጥር 011 551 0957 /011 557 6978 ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተ/ክለሃይማኖት ቅርንጫፍ ወረድ ብሎ ጎላ ፓርክ አጠገብ ተ/ክለሃይማት ጤና ጣቢያ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይቻላል።
በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ