በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያና የፅዳት ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን

የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡-

1. የጽህፈት መሳሪያና የፅዳት ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ

1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣

6. የጨረታ ዋስትና 20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፣

7. ጨረታውን ቢያሸንፉ ያሸነፏቸውን እቃዎችን ኬራቴ ከተማ በሚገኘው የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አምጥተው ማስረከብ የሚችሉ። ከሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኬራቴ ከተማ በመገኘት ተጫራቾች ለጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ-4 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው ከወጣ ከ15ኛው ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን 8፡30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 09-11-66-04-91/09-21–00–11-67

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

ኩራቴ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *