Your cart is currently empty!
በ300 ካ.ሜ ላይ የተሠራ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ማስታወቂያ
Yedebub Nigat(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሳሽ አቶ ይልቃል ታምሩ እና በአፈፃፀም ተከሳሾች 1ኛ/ ጥላ ማኑፈክቸርንግ አክሲዮን ማህበር በጠበቃ ጥላሁን ሉላየሁ እንዲሁም 2ኛ በአቶ አውግቸው ዘውዴ መካከል ባለው የብድር የገንዘብ ይመለስ ክርክር ጉዳይ በሰሜን B16p17 ፣ በደቡብ B16p29 ፣ በምስራቅ መንገድ ፣ በምዕራብ B16p10 የሚያዋስነው በጂንካ ከተማ ሊዝ መንደር በ300 ካ.ሜ ላይ የተሠራ መኖሪያ ቤት በካርታ ቁጥር 209/07 በ2ኛ ተከሳሽ ባለቤት በአቶ አውግቸው ዘውዴ ስም ተመዝግቦ የምገኘው መኖሪያ ቤት የጂንካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ባወጣው መነሻ ዋጋ ብር 1,942,423 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሁለት ሺህ አራት መቶ ሃያ ሦስት) ብር መነሻ ዋጋ መሠረት ተጫራች ካለ በጂንካ ከተማ አስ/ር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጨረታ ኮሚቴ ጋር በመቅረብ መጫረት የምችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዟል።
የጂንካ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት