Your cart is currently empty!
የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት የፅህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት እቃዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የመድረክ ዲኮርና ሙሉ ሳውንድ ሲስተም አገልግሎት እና ኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልጽ ጨረታ መግዛት እና በውል ለማሰራት ይፈልጋል
Addis Lessan(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት በጨረታ ቁጥር ል/ክ/ከ/ወ/9/ፋ/ጽ/ቤት/01/18
- የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፣
- የፅዳት እቃዎች፣
- የትራንስፖርት አገልግሎት፣
- የመድረክ ዲኮርና ሙሉ ሳውንድ ሲስተም አገልግሎት እና
- ኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልጽ ጨረታ መግዛት እና በውል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስተር በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በአጠቃላይ የእቃዎች ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ
- (ሎት 1)፦ የፅህፈት መሳሪያ 20000 (ሃያ ሺ ብር)
- (ሎት2)፦ አላቂ የቢሮ እቃዎች 4500 (አራት ሺ አምስት መቶ ብር )
- (ሎት3)፦ የፅዳት እቃዎች 20000 (ሃያ ሺ ብር)
- (ሎት4)፦ የደንብ ልብስ 20000 (ሃያ ሺ ብር)
- (ሎት5)፦ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና 5000 ( አምስት ሺ ብር)
- (ሎት6)፦ የመድረክ ዲኮርና ሳውንድ ሲስተም 2000 ( ሁለት ሺ ብር)
- (ሎት7)፦ የትራንስፖርት አገልግሎት 2000 ( ሁለት ሺ ብር)
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት በወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ፡፡
5. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ለማይቀርብላቸው እቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 401 ማስገባት አለባቸው።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት ካላካተተ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
8. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ በወጣበት 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በአስራ አንደኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 401 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
9. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚወዳደሩ አምራች ከሆኑ ለአምራችነታቸው የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን መወዳደር የሚችሉት በተደራጁበት ዘርፍ ብቻ መሆን አለበት፡፡
10. ወረዳው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ፣ ባልቻ ሆስፒታል ከፍ ብሎ ሶሊያና ህንጻ ፊት ለፊት
የወረዳ 9 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 011-869-3713/ 011-859 5404
በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት