Your cart is currently empty!
የቦታው ስፋት 171 ካ.ሜ. የሆነ መኖርያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Aug 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ሲሳይ ገ/ማርያም እና በፍ/ባለዕዳ እነ አለማየሁ ገ/ማርያም መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል በኮ/መ/ቁ/310986 በ30/04/2016 ዓ/ም እና በኮ/ መ/ቁ/315829 በ14/06/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ ከተማ ወረዳ 4 የሚገኝ የቤት ቁጥር 579 የሆነው በአመልካችና በተጣሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖርያ ቤት በቁጥር ል4/22/4190/01 የተመዘገበ የተነፃፀሪ ካርታ ያለው በፕሮፖርሽን ለግለሰቡ የሚደርሰው የቦታው ስፋት 171 ካ/ሜ ቤቱ (ቦታው) የሚገንበት አካባቢ ከዚህ ቀደም በጌጃ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የተያዘመሆኑ እስካሁን ያልተነሳ ሆኖ በባለሙያ ግምት የሐራጂ መነሻ ዋጋ ብር 5,948,721 (አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት ሽህ ሰባት መቶ ሀያ አንድ ብር) ሆኖ ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቅያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም፡፡ ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ16/9/2017 ዓ/ም ፍ/ቤቱ በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የግምቱን 1/4ኛ ብር 1,487,180.25 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሰማኒያ ሰባት ሽህ አንድ መቶ ሰማኒያ ብር 25/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 9፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4 አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ ዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻፀም ጽ/ቤት