የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኤሌከትሮ መካኒካል እቃዎችን ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

ፌ.ቤ.ኮ/ ብግጨ/ ዕቃ/ 10/12/2017

1. የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኤሌከትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤኮ/ ብግጨ/ዕቃ/10/2/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

2. ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚያገለግል የብረታ ብረት እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።

ተ.ቁ

የዕቃ ዝርዝር

የጨረታ ማስከበሪያ

1

የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ

50,000.00

3. ጨረታው የሚከናወነው ብበሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይህንኑ ኣስመልክቶ ከኢትዮዽያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።

4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 8 ቀን 2018 ዒ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል

6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

በስልከ ቁጥር 011-855 3617 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዌብሳይት /Website WWW.agh.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ. POBox 299/

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *