ጠቅላላ የይዞታ ስፋቱ 153 ካ.ሜ. የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Aug 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የፍ ባለመብት / መስቀሌ ግርማ እና የፍ/ባለዕዳ / መዓዛ በቀለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ /ቤት በመ/ቁጥር/110180 በህዳር 24 ቀን 2017 / እና በኮ///115105 6/5/2017 / በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ /ከተማ ወረዳ 12 ክልል ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 533 በይዞታ መለያ ቁጥር AA000091200418 ጠቅላላ ይዞታ ስፋት 153 / በባለሙያ ግምት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 6,235,722 (ስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ሁለት ብር) ሆኖ በሐምሌ 4 ቀን 2017 / በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቅያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም፡፡ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ /ቤቱ 29/11/2017 / በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የግምቱን 1/4 ብር 1,558,930.5 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰለሳ ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የተራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 29 ቀን 2018 / በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 930 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ//ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 330 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ// ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል /ቤቶች የፍርድ አፈጻፀም /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *