ፀደይ ባንክ አ.ማ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ እና የፅዳት ዕቃዎችን ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter(Aug 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ///0023/2017

ፀደይ ባንክ አማ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ እና የፅዳት ዕቃዎችን ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት ነጋዴ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።

  1. 2017 . የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርቲፊኬት፣ የታክስ ክሊራንስና የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸዉ ይገባል:: ቴክኒካል ዶክሜንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክሜንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ 90 ቀን በፀደይ ባንክ አማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል:: ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።
  3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከነሐሴ 26 ቀን 2017 . ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ 7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የባንኩ ዋና /ቤት 16 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ መሰከረም 08 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና /ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  5.  የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም
  6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911089281/0911383713

ፀደይ ባንክ አ.ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *