Your cart is currently empty!
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ እቃዎች፣ ስፔርፓርት እቃዎች፣ ምግብና መጠጥ፣ ኮስሞቲክስ ዕቃዎች፣ አልባሳት እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽና ሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ እቃዎች፣ ስፔርፓርት እቃዎች፣ ምግብና መጠጥ፣ ኮስሞቲክስ ዕቃዎች፣ አልባሳት እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 2/2018 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም፡– ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ለሀራጅ ጨረታ (ጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው።
2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ–ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ፣ በተራ ቁጥር 1 ከተገለጹት እና ሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና ፊርማ በግልጽ በመጻፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን 01/13/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
4. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ለኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን 01/13/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ላይ መገኘት አለባቸው።
5. ከላይ በተራ ቁጥር 3 እና 4 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም።
6. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ራሱን ከውድድር ውጭ ማድረግ አይችልም።
7. ለግልጽ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-3፡30 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 01/13/2017 ጠዋት 3፡30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ።
9. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ ጳጉሜ 01/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00-3፡30 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ።
10. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
1 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ |
እስከ 01/13/2017 ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ |
በ01/13/2017 ዓ.ም 3፡30 ተዘግቶ በእለቱ 3፡50 ሰዓት ይከፈታል |
2 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
ሐራጅ ጨረታ |
እስከ 01/13/207 ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ |
በ01/13/2017 ዓ.ም 4፡00 ይከፈታል |
11. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡– በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጂናል ይዘው መቅረብ አለባቸው።
12. ምድብ ለወጣላቸው ግልፅ እና ሃራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የአጠቃላይ እቃዎች ከፍተኛ ዋጋ ይሆናል።
13. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል።
14. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰበላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
15. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ የመረከብ እናለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል።
16. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊዉ የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ግቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቀጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
17. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታዉ መሳተፍ አይችሉም።
18. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተደደር የስራ ሂደት ስልክ ቁጥር 033-559-0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት