የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 01, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር /////01/2018

የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ለመግዛት ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የጨረታ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት-01

የደንብ ልብስ ግዥ

500,000.00

ሎት-02

የጽዳት ዕቃዎች ግዥ

500,000.00

ሎት-03

የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ

100,000.00

ሎት-04

የህንፃ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች ዕድሳትና ጥገና ግዥ

100,000.00

ሎት-05

የመድሃኒት ግዥ

300,000.00

ሎት-06

የሰፕላይና ሪኤጀንት ግዥ

300,000.00

ሎት-07

ህክምና መሳሪያዎች ግዥ

500,000.00

ሎት-08

የህክምና መሣሪያ እድሳትና ጥገና ግዥ

100,000.00

ሎት-09

የህክምና መሣሪያ መለዋወጫ ግዥ

100,000.00

በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ምርመራ
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚቸል
  4. ከገቢዎችና ጉምሩክ ስለ ግብር አከፋፈል ማስረጃ (ክሊራንስ) ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  5. በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት ለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው
  6. በመንግስት ግዥ ያልታገዱ
  7. የጨረታውን ማስረከቢያ CPO ብቻ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ CPO ኦሪጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 ብር በመክፈል በሆስፒታሉ የክፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር B-008 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ሆስፒታሉ በሰጠው በዝርዝር ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ብቻ በግልጽ መሙላት ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ስርዝ፣ ድልዝ ማህተም የሌለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  11.  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም የቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ ብሎ በመለየት በአራት (04) በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ፊርማና ማህተም ተደርጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 069 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  12. ጨረታው 10 ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የመክፈቻ እለቱ በበዓል ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  13. የጨረታ ማስከበሪያ በሎቱ በቀረበው መሰረት ነው።
  14. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈውን ስራ ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት CPO ማስያዝ አለበት።
  15. የሚገዙት ዕቃዎች በተሰጠው ስፔስፌስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው።
  16. አቅራቢዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው የጨረታ ቀኑ መጠናቀቂያ 10ኛው ቀን እስከ 1000 ብቻ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ናሙና ማስገባት አለባቸው። ናሙና ማስገባት ያለባቸው ፋይናንሻል ዶክመንት ላይ የተሞላ ዋጋን ብቻ ይሆናል። በተጨማሪም ለአንድ የአቅርቦት አይነት አንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
  17. አሸናፊው በራሱ ወጪ በማጓጓዝ እስከ ሆስፒታሉ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ አምጥቶ እና በራሱ ወጪ አውርዶ ማስረከብ አለበት።
  18. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ፡. የካ /ከተማ ወረዳ 04 ዳግማዊ ምኒልከ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
  • ለተጨማሪ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 011-123-42 72/ 011-126-02 80/ ይደውሉ

ዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *