Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን ሾኔ ከተማ አስ/ር የሾኔ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ጽ/መሣሪያ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 09, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን ሾኔ ከተማ አስ/ር የሾኔ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ጽ/መሣሪያ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራች ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው ያላት ፣ የዘመኑን የመንግሥት ሥራ ግብር የከፈለ/የከፈለች፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ያላት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ያላት፤ የተጨ.እ.ታ ምዝገባ VAT ተመዝጋቢ የሆነየሆነች የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ያላት፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሾኔ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ን/አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በብር 500.00 (አምስት መቶ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታውን ቴክኒካል ዋናውን ሰነድ እና ፋይናንሻል ዋናውን ሰነድ አንድ ላይ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻል ኮፒ እና ቴክኒካል ኮፒውን አንድ ላይ አሽጎ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪል ቀርቦ መወዳደር የሚችል መሆኑን እየገለጽን የጨረታው ሳጥን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ታሽጎ በዕለቱ 9፡00 ይከፈታል፡፡ የሚታሸግበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በCPO በባንክ በተረጋገጠ ቼክ፤ በባንክ በተረጋገጠ የዋስትና ደብዳቤ፤ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ለቀረበው የዕቃ ዝርዝር ዕቃውን የሚያቀርቡበትን ነጠላ ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ እንዲሁም በተሞላው ገጽ ላይ ፊርማ የድርጅቱን ማህተም ማስፈር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ በውል ወቅት ለሥራው በሚያስፈልገው ዕቃ መጠን ይባዛል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ቫት የሚያካትትና የማያካትት መሆኑ በትክክል መገለፅ አለበት። ቫት በትክከል ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫት እንዳካተተ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡
- አሸናፊ አቅራቢ የሚለየው ቴከኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡ በዚህ መሠረት ለተጠየቁ ለሁሉም ዕቃዎች ዝርዝር ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ለሾኔ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል/በህጋዊ /ወኪል በኩል በመቅረብ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የቀረበ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ኤንቨሎፑ ሳይከፈት ለተጫራች ተመላሽ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ መስፈርቶች በጨረታ ሠነድ ውስጥ በጨረታ መገምገሚያው መስፈርት መሰረት ይገመገማል፡፡
- የተለየ ዕገዳ ያለበት ተጫራች ከውድድሩ በቀጥታ ይሰረዛል፡፡
- መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– 09 10 80 60 12/ 09 11 91 80 05/
የሾኔ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት