በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ለጀነሬተር እና ለተለያዩ ሞተር ሳይክሎች ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 08, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/2017-2018

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ //ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡

  • ሎት1. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት2. ለጀነሬተር እና ለተለያዩ ሞተር ሳይክሎች ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው፤

4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5. የግዢው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራቹን ስም፣ የተመረተበትን . በዝርዝር ከዋናው ጨረታ ሰነድ ጋር መያያዝ አለበት፣

8. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለባቸው፣

9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለጀነሬተር እና ለተለያዩ ሞተር ሳይክሎች ብር 50,000/ሃምሳ ብር/ እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 30,000/ሰላሳ ብር በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 – 6 የተጠቀሱትን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን /መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣

11. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን /መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጉራጌ ዞን /መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/ አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 1130 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡

12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፡፡

13. /ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. ለበለጠ መረጃ /ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-330-0112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት እንገልፃለን፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ