Your cart is currently empty!
በቂርቆሰ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2018 በጀት መገልገያ የሚሆኑ የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 08, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለቢሮ አገልገሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ግዥ
ለመፈፀም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0020/2018
በመ/ቤታችን በቂርቆሰ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2018 በጀት መገልገያ የሚሆኑ
- ሎት 1 የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣
- ሎት 2 የተለያዩ የህክምና የLARATORY ቋሚ ዕቃዎችና መድኃኒቶች፣
- ሎት 3 ጎሚስታ አገልግሎት እና የመኪና እጥበት አገልግሎት፣
- ሎት 4 የተለያየ የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች፣
- ሎት 5 የተለያዩ የአሻራ ፓውደር፣
- ሎት 6 የተለያዩ አልባሳት፣
- ሎት 7 የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 8 የተለያዩ የህትመት ሥራዎች፣
- ሎት 9 የተለያዩ የመመገቢያ ዕቃዎች፣
- ሎት 10 የአይሲቲ ዕቃዎች፣
- ሎት 11 ስፖንጅ ፍራሽ ከነትራሱ፣
- ሎት 12 የተለያዩ ሰነድ ማስተርጎም፣
- ሎት 13 የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ክበብ አገልግሎት፣
- ሎት 14 ID CARD MATERIAL ማተሚያ ማሽን፣
- ሎት 15 የመኪና ከሬን ማንሻ እና አይሱዙ የመኪና ኪራይ አገልግሎት፣
- ሎት 16 የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ኪራይ
- ሎት 17 የመኪናዎች ሸራ ከነ መወጠሪያ ብረቱ፣
- ሎት 18 የቢሮ የምንጣፍ ማፅጃ ማሽኖች ፤
- ሎት 19 ለተሸከሪካሪ እና ለህንፃ ድንገተኛ እሳት ማጥፊያ ፎም፣
- ሎት 20 የቀን ጉልበት ሰራተኛ ኮንትራት
- ሎት 21 የገንዘብ ማስቀመጫ ካዝናዎች፣
- ሎት 22 የዳቦ መጋገሪያ አገልግሎት የሚውሉ ፓትራዎች ፣ የዳቦ ሊጥ ማቡኪያ ማሽን እና የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ጥግና
- ሎት 23 ችፑዶች፣
- ሎት 24 የፖሊስ መኖሪያ ካምፕ እና የተለያዩ የቢሮዎች ጥገና፣
- ሎት 25 Core i7 ላፕቶፕ በጨረታ አወዳድሮ ለ2018 ዓ ም መገልገያ የሚሆኑ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡–
1. ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፤
2. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፤
3. የዘመኑን የንግድ ፈቃድ የነበሩ ስለመሆናቸው ወይም ስለመታደሱ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት እንዲሁም የግብር ከፋይ ውሉን 41 አራት በአንድ ማቅረብ የሚችል
4. ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. በሚጠየቀው መሠረት ለጨረታ የተወዳደረበትን ጥራት ያለው ያሽነፈበትን ዕቃ በተሰጠው የጊዜ ገደብና ተወዳድሮ ባሸነፈበት በውሉ መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፤
6. የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች የከበብ ምግብ እና ትኩስ ነገር አቅርቦት ላይ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ አይገደዱም አንዲሁም ለመድሃኒቶችና ለምግብ በገቢዎች መመሪያ መሠረት ተጨማሪ እሴት ታክስ ሠርተፊኬት ማቅረብ አይገደዱም።
7. በሎት 24 የፖሊስ መኖሪያ ካምፕ እና የተለያዩ የቢሮዎች ጥገና እንዲሁም የህክምና Laboratory ቋሚ ዕቃዎችና መድኃኒቶች ላይ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይገደዳል።
8. ጨረታውን መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቅዳሜ እና እሁድ ሳያካትት 10 የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር በሎት 400 አራት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛትና ለጨረታ ሰነዱ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው በዚያኑ እለት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃዎች
- ሎት 1. 1000.00 ብር
- ሎት 2. 5,000.00 ብር
- ሎት 3.500.00 ብር
- ሎት 4.2000.00 ብር
- ሎት 5. 2000.00 ብር
- ሎት 6. 1,000.00 ብር
- ሎት 7.1.500.00
- ሎት 8. 2,000.00
- ሎት 9. 5,000.0
- ሎት 10. 5,000.00
- ሎት 11. 5,000.00
- ሎት 12. 3000.00
- ሎት 13. 500.00
- ሎት 14.10,000.00
- ሎት 15. 1,000.00
- ሎት 16. 1,000.00
- ሎት 17. 2,000.00
- ሎት 18. 2000.00
- ሎት 19. 1,000.00
- ሎት 20. 1,000.00
- ሎት 21. 2,000.00
- ሎት 22. 2000.00
- ሎት 23 2,000.00
- ሎት 24 5,000.00
- ሎት 25, 20,000 የጨረታ ማስከበሪያ በየሎት በጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ ከተደራጁበት ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. አሸናፈው ተለይቶ እንደታወቀ በጨረታው ለተሳተፉት ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
11. መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ናሙና ያሚያስፈልጉት የዕቃ አይነቶች ተጫራቹ ጨረታው ከመዘጋቱ ቀደም ብለው የናሙናውን አይነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ናሙና ለማይቀርባቸው የዕቃ አይነቶች በሚቀርበው የዕቃ መግለጫ /specification/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከላይ በተዘረዘሩት መሠረት ለመወዳደር የምትፈልጉ እና በሚቀርበው ውል መሠረት በማቅረብ በደንቡ መሠረት መጫረት የምትችሉ መሆኑን በግልጽ በማመልከት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
አድራሻ፦ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ላይ የቀድሞው ስፖርት ፌዴሬሽን ህንፃ 5ኛ ፎቅ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ