በቂርቆስ ከፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የጠመንጃ ያዥ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት መረጃ መሳሪያዎች፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የጥገና ሥራዎች ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 09, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ከፍለ ከተማ ትምህርት /ቤት የጠመንጃ ያዥ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 2018 . በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ፡ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፡

  • አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
  • አላቂ የትምህርት መረጃ መሳሪያዎች
  • የሰራተኞች የደንብ ልብስ
  • የጥገና ሥራዎች

1. የተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. የጨረታ ማስረከቢያ 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች በጠመንጃ ያዥ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 02 በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ 1 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።

8. ጨረታው 10ኛው ቀን ከቀነ 11:00 ተዘግቶ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ከጠዋቱ 330 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል።

9. አሸናፊዎች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች እስከ ትምህርት ቤቱ ግማጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የተሰረዘ፣ የተደለዘና ግልፅነት የሌለው ጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።

12. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመጫረቻ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርበታል።

  • ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 011 470 3882
  • አድራሻ፡/ዘይት መንገድ በጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንክ ፊትለፊት በእምነት ሬስቶራንት ጀርባ 200 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
  • ስልክ ቁጥር፡-011 466 1301 ..ቁ፡-100768
  • ኢሜል፡ temnayaleprimaryschool@gmall.com   

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት /ቤት የጠመንጃ ያዥ ቅድመ

አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት