በአብክመ በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለግ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት የጽሕፈት መሣሪያ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 001/18

በአብክመ በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለግ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት የጽሕፈት መሣሪያ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድና ምዝገባ፣ ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል፣
  2. የግዥ መጠኑ ከ200,000 ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆነና መረጃ ማቅረብ የሚችል።
  3. ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ (ማስገባት) አለባቸው።
  4. የሚገዙ ዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ግ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢ.ቁ 20 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች በዝርዝር በተገለጸው እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ግ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሚወዳደሩበት ዕቃ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በቁርጥ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ በመቁረጥ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታ ውስጥ አሽጎ (አያይዞ) ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ዋጋው ጸንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለ40 /አርባ ተከታታይ ቀናት/ ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል።
  7. ጨረታው ተጫራቾች |ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  8. አሸናፊ ተጫራች ውጤቱ በማስታወቂያ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ቀን ድረስ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሌተር ኦፍ ክሬዲት በማስያዝ ከግ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ ለማስረከብ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል። የሚገዙት ዕቃዎች የማስረከቢያ ቦታ ግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ባሉ ንብረት ክፍሎች ውስጥ ሆኖ ለኮምፒውተር ቀለሞች አንድ ዓመት የሚቆይ ጋራንት ማስያዝ አለበት።
  9. ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተጫራቾች መመሪያም ተያይዟል፤ ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ካስፈለገ በጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0332120300 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለ።

በአብክመ ስ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገንዘብ ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *