Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
(የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፈ/ህ/ጤ/ጣ/ 001/2017)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ የተለያዩ ህትመቶች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስና የደንብ ልብስ ስፌት፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፤ የሰራተኞች መመገቢያ የካፌ አገልግሎት፤ የኮምፒዩተር፤ የፎቶ ኮፒ፤ የላፕቶፕ፣ የጄኔሬተር ሰርቪስና ጥገና፤ የበር፤ የመስኮት፣ የውሃ ቧንቧ ሲበላሽ የጥገና አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው፣
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላችሁ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ሊስት ውስጥ የተመዘቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፤
- የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛትና የጨረታ ሰነዱን በትክክል በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናን በሚመለከት ተጫራቾች በሚወዳደሩበት አቅርቦት ላይ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ
|
የእቃው አይነት በሎት
|
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ወይም ቅድመ ሁኔታ ባስቀመጠው የባንክ ዋስትና |
|
ሎት 1 |
ህትመት |
3000.00 |
|
ሎት2 |
የጽህፈት መሳሪያዎች |
2000.00 |
|
ሎት3 |
የጽዳት እቃዎች |
2500.00 |
|
ሎት4 |
የደንብ ልብስና የደንብ ልብስ ስፌት |
3000.00 |
|
ሎት5 |
የፎቶ ኮፒ ማሽን፤ የኮምፒዩተር፣ የፕሪንተር ሰርቪስና ጥገና፣ |
2500.00 |
|
ሎት6 |
የጀኔሬተር ሰርቪስና ጥገና፣ የበር፣ የመስኮት፣ የውሃ ቧንቧ ሲበላሽ ለመጠገን |
3000.00 |
|
ሎት7 |
የኤክትሮኒክ እቃዎች |
5000.00 |
|
ሎት8 |
የመድሀኒት እስቶር ዲስፓች ኤርያ የላቦራቶሪ ከፍል መስኮት የመስታወት ስራ፤ የአሉሚኒየም በር ስራ፤ የላቦራቶሪ ከፍል ወለል ሙሉውን EPOXY የቀለም ስራ፤የጄኔሬተር ከፍል የጣሪያ እድሳት፣ ጤና ጣቢያው ህንጻ ላይ በላሜራ የሚሰራ አዳራሽ ስራ የመብራት መስመር ዝርጋታ፤ |
5000.00 |
- የተሸናፊዎች የጨረታ ማስከበሪያ በ15 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ ባሸነፈው ዋጋ ልክ 10% ያስይዛሉ፤
- ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰአት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአትና ቀን ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው ቀን ከጣዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰአት የሚከፈት ሲሆን አስራ አንደኛው ቀን ግን ቅዳሜና እሁድ ወይም የባዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው ከፍያ ሂሳብ ከፍል የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ናሙና ማቅረብ ያለባቸውን ፍላጎቶች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
ማሳሰቢያ፡– የጨረታ ሰነዱን ስታስገቡ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሁለት ፖስታ አሽጋችሁ ማስገባት አለባችሁ፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን ማስረጃዎቻችሁን በኮፒው የጨረታ ሰነድ ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ።
አድራሻ — ወረዳ ጎተራ ኮንዶሚኒየም አጠገብ ከሀሌ ሉያ ሆስፒታል ጎን፤
በስልክ ቁጥር– 01186681224/20
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና/ጽ/ቤት የፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ