Your cart is currently empty!
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር APPF/NCB/01/18
1. በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ–ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- LOT 1. የተለያዩ የምርት ማሸጊያዎች
- LOT 2, የIT (information Technology) ዕቃዎች
- LOT 3. የፅህፈት መሳሪያ (Stationary) ዕቃዎች
- LOT 4. የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች
- LOT 5. የተለያዩ ተሽከርካሪ ጎማዎች (TYRE FOR DIFFERENT VEHICLES)
2. ተጫራቾች የስራ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ለሚከፈልባቸው ዕቃዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በመንግሥት የግብር ሕግ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ሰርተፍኬት እና በመንግሥት ግዥ ለመሳተፍ በመንግስት የኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ፖርታል ላይ በአቅራቢነት መመዝገቡን የሚያሳይ መረጃ እንደ ቅድመ ሁኔታ ማቅረብ ይኖባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኢምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ጅቡቲ ኢምባሲ ፊት ለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር አምስት መቶ ብቻ (500.00) በመክፈል ጨረታው ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ድርጅት ስምና አድራሻ በትከክል ተፅፎ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
5. በ LOT 1 እና LOT 2 ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነዶቻቸውን ኮፒ እና ኦርጅናሉን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከLOT 3 እስከ LOT 5 ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በተጫራቹ ድርጅት ኃላፊ ተፈርሞና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ–ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ስም የባንከ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው የቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን እስከ መስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የፋብሪከው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ መከፈቻው እለት መስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቦሌ ርዋንዳ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ይሆናል፡፡
9. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ አ.አ ማስተባበሪያ ስልከ ቁጥር 011 662 4656 አ/አ ፣ አዳሚ ቱሉ 046 441 9164(ማዞሪያ)፤ 046 841 0447(ንግድ መምሪያ) ፖ.ሣ.ቁ 1206 (አ.አ)፣ 247 (አ/ቱሉ)
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ–ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ