Your cart is currently empty!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ -11 አስተዳደር የረጲ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ -11 አስተዳደር የረጲ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ማለትም፣
- ሎት1 አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት3 መፅሃፍና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
- ሎት4 እድሳትና ጥገና ዕቃዎች፤
- ሎት 5 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 6 የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት7 የማሽነሪ ቋሚ እቃ፣
- ሎት8 ህንፃ ቁሳቁስ ፣
- ሎት8 የጥገና ስራዎች፤
- ሎት10 የላብራቶሪ እቃዎች
- ሎት11 ልዩ ልዩ እቃዎች
- ሎት 12 የህትመት ስራዎች፣
- ሎት13 የመምህራን መዝናኛ ካፌ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ
1. በመንግስት እቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ያለው፡፡
2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ለተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300,00/ሦስት መቶ/ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከአል–ሰላም ዳቦ ቤት ወይም ታከሲ ተራ 100ሜ አለፍ ብሎ በረጲ የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር -03 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ ቀናት በተጠቀሰው የቢሮ ቁጥር በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ናሙና ወይም ስነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
6. አንዱ በለጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
7. ገዢው በአካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል::
8. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ እና መደበኛ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛ ቀን ከጥዋቱ 2፡30 ሰዓት ታሽጓ ከጥዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡
10. ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሎት1፣ ሎት2፣ሎት3፣ሎት4፣ሎት 5ሎት፣6 ሎት7፣ሎት8 ብር 35,000 / ስላሳ አምስት ሺ ብር/ እንዲሁም ሎት09፣ ሎት10፣ ሎት11 ሎት12 ሎት 13 ሎት 10,000 ብር /አስር ሺ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ/ሲፒኦ/ ተጫራቶች ማስያዝ ያኖርባቸዋል፡፡አሸናፊው ድርጅት ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙትን ሲፒኦ /C.PO/ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
11. የእቃው ማስረከቢያ ቦታ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ በረጲ የመጀ/ደ/ት/ቤት ንብረት ክፍል ይሆናል
12. በሚቀርበው በመወዳደሪ ሃሳብ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ስምና ፊርማ፣ የድርጅቱ አድራሻ፣ የድርጅቱ ማህተም እና የስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡
13. ት/ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 8 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ከ7ተኛው ቀን ቀጥሎ ውል መፈፀምና 10%የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /C.P.O/ ማስያዝ አለበት፡፡
15. የእቃ ማጓጓዣ አሸናፊው ድርጅት ይሸፍናል።
16. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡– በኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 11 የረጲ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ሲሆን
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡–
- 011-369-4040
- 011-369-3994
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ
ከተማ ወረዳ -11 አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የረጲ የመጀ/ደ/ት/ቤት