በደቡብ ምዕራብ ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዘመን በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ገዥዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 04, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ምዕራብ //ክልላዊ መንግስት የካፋ ዞን ከፍተኛ /ቤት 2018 በጀት ዘመን በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ገዥዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም የግዥ ማዕቀፎች በተመለከተ የሚከተሉ ይሆናሉ፡

  • ሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት ማሳሪያዎችና የፅዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 2 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • ሎት 3 የመኪና ጎማ፣
  • ሎት 4 ለመ/ቤቱ ዳኞችና በጉባኤ ለሚተዳደሩ ሠራተኞች የሠርቪስ አገልግሎት የሚሠጥ የመኪና ኪራይ ሲሆን በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እና በሰነዶች የተገለፁትን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስተናገድ ይፈልጋል።

1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከካፋ ዞን ከፍተኛ /ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ላይ ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

3. ለመኪና ሰርቪስ ኪራይ የሚሳተፉ ተጫራቾች የመኪና ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው መኪናው እንሹራንስ ስለመግባቱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

4.ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት አንድ ኮፒ እና አንድ ኦሪጅናል በታሸገ ኤንቨሎፕ በካፋ ዞን ከፍተኛ /ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 10,000/አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።

6.የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈዉን ዕቃ /ቤቱ ለይቶ ካሳወቀበት ሰዓት ጀምሮ ዉል ከመግባቱ በፍት ያሸነፈዉን የዕቃ ናሙና እስከ /ቤቱ ድረስ በማቅረብ በጥራት ኮምቴ አስገምግሞ ተቀባይነት ያገኙ ዕቃዎችን ለኮሚቴ በአደራ አስቀምጦ መሄድ መቻል ይኖርበታል።

7.የጨረታዉ አሸናፍ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ ካፋ ዞን ከፍተኛ /ቤት ድረስ በመገኘት ዉል በመግባት ወል ከገባበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 07 ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን ሙሉ ዕቃ /ቤት ድረስ በማቅረብ ቆጥሮ ማስረከብ መቻል አለበት፣ ሆኖም አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ ጥራቱና መጠኑ የተጓደለ ከሆነ በራሱ ኪሳራ መቀየር የሚችል መሆን ይኖርበታል።

8. የጨረታ መዝጊያው ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 16 ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 430 ሰዓት ላይ ይከፈታል ሆኖም የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም።

ማሳሰቢያ፦ /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ይሆናል።

በደቡብ ምዕራብ //ክልላዊ መንስት የካፋ ዞን ከፍተኛ /ቤት