በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጎፋ ዞን በቡልቂ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዓይነት ጽህፈት መሳሪያ፣ የተለያዩ ዓይነት ህንፃ መሳሪያ፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ በንጥል ዋጋ አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጎፋ ዞን በቡልቂ ከተማ አስተዳደር  ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት

  1. በሎት አንድ የተለያዩ ዓይነት ጽህፈት መሳሪያ
  2. በሎት ሁለት የተለያዩ ዓይነት ህንፃ መሳሪያ
  3. በሎት ሶስት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ በንጥል ዋጋ አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል። 

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።

  1.  በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ
  4. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ ያላቸው
  5. ተጫራቾች የዘመኑን የአንድ ዓመት ታከስ ክሊራንስ /TAX CLEARANCE
  6. የአቅራቢነት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ CPO በጥሬ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ በየሎቱ ለየብቻው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ከላይ 1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል።
  9.  የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቡ/ከ/አስ/ር ገቢዎች ቢሮ በመቅረብ ለዚህ የተዘጋጀውን ጨረታ ሠነድ ያገኛሉ።
  10. የጨረታ አሸናፊው ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ እስከ ቡልቂ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል አምጥቶ በጨረታ ሠነዱ መሠረት መሆኑን በጥራት አረጋጋጭ ኮምቴ አስፈትሾ ማስረከብ አለበት።
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው የመንግስት ሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ጨረታው ይከፈታል። 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል
  12. የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በመንግስት ሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 10፡30 ይሆናል።
  • ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 09 25 14 25 21 / 09 27 05 83 19/ 09 27 53 43 31) ይደውሉ።

በደ/ኢ/ክ/መ በጎፋ ዞን ቡልቂ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት