Your cart is currently empty!
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 1/2018
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ ለመሳተፍ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ ንግድ ፈቃድ የዘመኑ ግብር ተከፍሎ የታደሰ፣ ቲን ቁጥር ሴርተፊከት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ያለውና የሚያቀርብ፣
- ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-8
- ተፈላጊ የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን የሚያቀርቡበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ፕሮፎርማ ሞልቶ ከተፈላጊ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ጋር በፖስታ አሽጎ የሚያቀርብ
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 50 /ሃምሳ ብር ብቻ/ ለኮሬ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዩኒት በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ሚያበቃበት ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-8 መውሰድ ይቻላል።
- የጨረታ ሣጥን የሚታሽግበትና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በተመለከተ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ወደ ፊት የሚቆጠር በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽገው በዕለቱ በ8፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በሳምንት ዕረፍት ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ይፋ ከሆነበት ዕለት ጀምሮ ለ5 የሥራ ቀናት ለቅሬታ አቤቱታ ጊዜ ሰጥቶ ከ8ኛው እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውል ካልተፈራረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ውርስ በማድረግ ለአፈፃፀሙ ለክልል ግዥ ኤጀንሲ ሪፖርት እናደርጋለን።
- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ / በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ የሚያስይዝ መሆን አለበት።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃዎችን ሁሉንም ወጪ ችሎ እስከ ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ መጋዘን ድረስ አቅርቦ ማስረከብ አለበት።
- በጨረታ ሰነድ ላይ ናሙና የሚጠይቁትን ዕቃዎችንና ሌሎችም ያልተጠየቁትም ኦሪጅናልና 1ኛ ደረጃ ትክከለኛ ማቅረብ አለበት።
- የተጫራቾች ተሟልተው አለመገኝት የጨረታ ሂደትን አያስተጓጉልም።
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በጥራት 1ኛ ደረጃ መሆን አለበት፤ አቀላቅሎ የሚያቀርብ ካለ እንደ ተጨበረበረ ተቆጥሮ በክልል ግዥ ኤጀንሲና በህግ እርምጃ እንዲወሰድበት ይደረጋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ፡- 0464570452/ 0916130084
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ