Your cart is currently empty!
በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስና የጽህፈት መሣሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 04, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
1ኛ ዙር ማስታወቂያ
በደቡብ ኢ/ክ/ መንግሥት በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክትር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒከስና የጽህፈት መሣሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የተጫራቾች መስፈርቶች ፡–
1 በዘርፉ በ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋብነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
3. የዘርፉ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
4. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
5. በመንግስት ግዥ አቅራብነት የተመዘገበ፣
6. የግዥ ኤጀንሲ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ዕገዳ ያልተጣለበት፣
የተጫራቾች ግዴታዎች፡–
7. ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 ያሉ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብርና ሰነድ በመግዛት ለዚህ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8.ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ዕቃ በራሱ ወጪ እስከ ደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግቢ ማቅረብ አለበት፣
9. ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብ አለበት፣
10. ናሙና የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ለመ/ቤቱ በቅድሚያ ማቅረብ አለበት
11. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00/አምስት ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ እውቅና ካለው ባንክ ማስያዝ አለበት።
12. የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ የግዥ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ cpo ማቅረብ የሚችሉ።
13 ለአሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ እስከ ኛው ቀን ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል ማግባት አለበት።
14 የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
15. የጨረታ ሰነድ ከደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመግዛት የገዙትን ሰነድ በመሙላት የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ዋናውና ኮፒው በሁለት ለብቻ አሽጎ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛውን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ የሚከፈተው ከታሸገበት 30 ደቂቃ በኃላ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሰነድ የመከፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም።
ማሳሰቢያ፡–
16. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
17. መ/ቤቱ ሌላ የተሻለ ለማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
18. ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን ዕቃ ዋጋ የማቅረቢያ ሰነድ የተጠቀሰውን ዕቃ ሙሉ በሙሉ መሙላት።
በደቡብ ሲ/ክ/ መንግሥት በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት