Your cart is currently empty!
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጠቅላላ ሆስፒታል የመድሃኒት እና ልዩ ልዩ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ የምግብ ግብዓቶች፣ የደንብ ልብስ፣ የጥገና ዕቃዎች፣ ህትመት፣ የፅዳት እቃዎች፣ የፅህፈት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 09, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ/008/2018 ዓ.ም.
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ ቀጥሎ በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት አንድ (01) የመድሃኒት እና ልዩ ልዩ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣
- ሎት ሁለት (02) የምግብ ግብዓቶች
- ሎት ሶስት (03) የደንብ ልብስ፤
- ሎት አራት (04) የጥገና ዕቃዎች፣
- ሎት አምስት (05) ህትመት፣
- ሎት ስድስት (06) የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት ሰባት (07) የፅህፈት ዕቃዎች፣
በዚህ መሰረት፡– በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣
- የንግድ ስም የምስክር ወረቀት፣
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤
- በግዥ ኤጀንሲ ድረ–ገፅ www.ppa.gov.et / በአቅራቢነት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ጉምሩክ ባለ ስልጣን የተፃፈ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ እቃ ናሙና ሳንፕል /ለሚያስፈልጋቸው ናሙና በአግባቡ መዝገበው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ከሆነ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የታደሰ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት
- የተለያዩ መዲኃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች መስከረም 20 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 5፡00 ይከፈታል፡፡
- የምግብ ግብዓቶች መስከረም 21/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የደንበ ልብስ በዚሁ ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተዘግቶ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- የተለያዩ የጥገና እቃዎች መስከረም 22 ቀን/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፤
- ህትመት በዚሁ ቀን ከቀን 7፡00 ተዘግቶ 7፡30 ይከፈታል፡፡
- የፅዳት እቃዎች መስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ 5፡00 ይከፈታል፡፡
- የፅህፈት እቃዎች በዚሁ ቀን ከቀኑ 7፡30 ተዘገቶ 8፡00 ሰዓት በፌዴራል ማረ/ቤት ኮ/ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200/ሁለት መቶ ብር/በመክፈል በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጠቅላላ ሆስፒታል በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ አካውንት ቁጥር 1000007971568 ገቢ በማድረግ ህጋዊ የባንክ ደረሰኝ እያቀረቡ የጨረታውን ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳ ሎት ማለትም ለሎት 1፡ 1100000/መቶ ሺ ብር፣ ለሎት 2፤3፤4፤5፤6፡7 ደግሞ 20,000 ሃያ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዮ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፤– ቃሊቲ ሽገር ዳቦ ቤት ጎን ፌዴራል የማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጠቅላላ ሆስፒታል።
ለተጨማሪ መረጃዎች: በስልክ ቁጥር 09 47 23 22 33 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጠቅላላ ሆስፒታል
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Chemicals and Reagents cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Food Items and Drinks cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx Health Care, cttx Pharmaceutical Products cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Products and Services cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Raw Materials and Supplies cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Medical Industry cttx