Your cart is currently empty!
ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ለሚገኙ የጤና ተቋማት በድጋፍ መልክ የሚሰጥ የሕክምና ዕቃዎችና የኬሚስትሪ ማሽን ሪኤጀንቶችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች/ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Reporter(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሕክምና ዕቃዎች እና የኬሚስትሪ ማሽን ሪኤጀንቶች ግዥ ጨረታ
ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ለሚገኙ የጤና ተቋማት በድጋፍ መልክ የሚሰጥ የሕክምና ዕቃዎችና የኬሚስትሪ ማሽን ሪኤጀንቶችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች/ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
በመሆኑም በዘርፉ የተሠማራችሁና በጨረታዉ ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡–
- በበጀት ዓመቱ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸሁ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ቲን ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸሁ፣
- በዘርፉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ድርጅቶች/ ነጋዴዎች
ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 07 (ሰባት) ቀናት የጨረታ ሠነዱን በብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ቀይት ከሚገኙ የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በመግዛት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 1% ከባንክ ሲፒኦ ጋር በፖስታ አሽጎ በማስገባት እንድትወዳደሩ እየጋበዝን ጨረታዉ በ8ኛዉ ቀን በ5፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ5፡30 ሠዓት የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን 8ኛዉ ቀን በካላንደር የሚዘጋ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳዉቃለን::
ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
ተስፋ ብርሃን ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
ደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር
ጣይቱ ክፍለ ከተማ
ቀይት ቀበሌ
ለተጨማሪ መረጃ
ስ.ቁ 011-656-0249 ወይም