Your cart is currently empty!
አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የቪድዮ ኮንፍረንስ ሲስተም ማተሪያሎችን ከነ ሙሉ አክሰሰሪአቸው (Video Conference System Materials with full Accessories) መግዛት ይፈልጋል
Reporter(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት፣ በጤና እና በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው።
በመሆኑም ማህበሩ ለዙም አገልግሎት የሚውሉ የቪድዮ ኮንፍረንስ ሲስተም ማተሪያሎችን ከነ ሙሉ አክሰሰሪአቸው (Video Conference System Materials with full Accessories) መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡–
- የእቃዎቹን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ቦሌ መንገድ ከቦሌ መተሚያ ቤት ጐን በሚገኘው አዲስ አበባ አልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ማግኘት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረተው እቃ ማስከበሪያ ዋስትና 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ለእቃው በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል አዲስ አበባ በሚገኘው አልማ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፣
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አዲስ አበባ አልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ተዘግቶ በእለቱ በ9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 203 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 551 2528/ 011 551 7886 በመደወል ማግኘት ይችላ።