Your cart is currently empty!
ኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚ/ር በሰላም ማስከበር ማዕከል በድሬዳዋ አከባቢ የሚገኘው ሁርሶ ኮንቲጀንት ማ/ት/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር፡-CON/TRS/ ANNUAL PROCUREMENT 001/2018
ግዥ ፈፃሚው ኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚ/ር በሰላም ማስከበር ማዕከል በድሬዳዋ አከባቢ የሚገኘው ሁርሶ ኮንቲጀንት ማ/ት/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1የኛ ዙር ግዥ ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ጋር ዝርዝራቸው ከዚህ በታች በየሎቱ የተገለፁትን የዕቃ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የሚገኙት የዕቃ ዓይነቶች በየሎቱ ምድቡ በተሰጠው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ከታች የተገለፁትን መስፈርቶችን የምታሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ።
1. ሎት አንድ የተለያዩ አልባሳትና ተዛማጅ ዕቃዎች -16,000.00
2. ሎት ሁለት የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች -16,000.00
3. ሎት–ሶስት የተለያዩ የፅዳትና ተዛማጅ ዕቃዎች -40,000.00
4. ሎት አራት የተለያዩ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 5,000.00
5. ሎት አምስት የተለያዩ የህንፃ መሳሪያ እና ተዛማጅ ዕቃዎች 19,300.00
6. ሎት ስድስት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች 28,000.00
መመዘኛዎች፡–
ከላይ በየሎቱ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ለማቅረብ ብቃት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን መመዘኛ የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታ መሳተፍና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ማሰልጠኛ ት/ቤቱ በደስታ ይጋብዛል።
1. ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነስርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
2. በዘርፉ የተሰማሩበት የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ፣ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ቲንነምበር፣ ቫት ተመዝጋቢ፣ የንግድ ፍቃድና የዘርፍ በግልፅ በጀርባው ዝርዝር የተገለፀ መሆን አለበት። እንዲሁምጨረታ ለመወዳደር የተሰጠ ፍቃድ ማስረጃ ኦርጅናሉና ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ኦርጅናሉ ተመሳክሮ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
3. ተጫራቾች ከላይ በየሎቱ የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በተወዳደሩበት ሎት ከባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ስም የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
4. የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 28/12/2017 ጀምሮ እስከ ሚከፈትበት ቀን 07/01/2018 ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት በድሬዳዋና አካባቢው የምትገኙ በሁርሶ ኮንቲጀንት ማ/ት/ቤት በፋይናንስ ዴስክ ገንዘብ በመክፈል ከግዥ ዴስክ ቢሮ ቁጥር 26 ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛትና መውሰድ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም በአ አበባና አካባቢው የምትገኙ ጃን ሜዳ በሚገኘው የሠላም ማስከበር ማዕከል ፋይናንስ ቡድን ገንዘብ በመክፈልና ሰነዱን ከግዥ ቡድን ቢሮ በመሄድ የጨረታ ሰነድ መግዛትና መውስድ ይችላሉ።
5. ጨረታው ፕሮፎርማ ታሽጎ ፊርማ፣ ማህተም፣ ስልክ ቁጥርና አድራሻ ተደርጎበት ኦርጅናልና ኮፒ በመባል ለየብቻው በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የሚወዳደሩበት ሎት በመጥቀስ የግዥ ፈፃሚ አድራሻ በማስቀመጥ የጨረታ መክፈቻ ቀን ጠዋት 2፡00 እስከ 8፡15 ሠዓት ድረስ ለጨረታ ወደ ተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ 8፡15 ታሽጎ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በ8፡30 ሠዓት ድሬዳዋ ነምበር ዋን መኮንኖች ክበብ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ፊርማቸው፣ስማቸው፣አድራሻቸው፣ስ ቁጥራቸው፣ዋጋ ማቅረቢያው ለስንት ቀን፣ወር እንደሚያገለግል፣መግለፅና ማስፈር አለባቸው።
7. የውል ማስከበሪያ ከአሸነፉት ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
8. የጨረታ መክፈቻ በስራ ቀን ካልዋለ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል።
9. አሽናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት (ወጪ) ሸፍኖ ሁርሶ ኮንቲጀንት ማ/ት/ ቤት ግቢው ስቶር ድረስ የንብረት ክፍሉ ገቢ ማድረግ አለበት።
10. ተጫራቾች የዕቃው ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ናሙና ይዞ መቅረብ ናሙና ማቅረብ የማይቻልባቸው ደግሞየሚያቀርቡት ዕቃ በፎቶ ግራፍና ካታሎግ አስደግፎ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የዕቃ ስፔስፊኬሽን እናየጥራታቸው ደረጃ በግልፅ መገለፅ አለባቸው።
11. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ መ/ቤታችን በሚሸጠው ሰነድ ላይ ዋጋ መስጠት አይቻልም ዋጋ መስጠት የሚችሉበራሳቸው (በድርጅቱ) ስም በተዘጋጀው ፕሮፎርማ ላይ ሲሆን መ/ቤታችን በሚሸጠው ሰነድ ላይ ዋጋ የሞላተወዳዳሪ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
12. በዕለቱ የጨረታ ሳጥን ከታሸገ (ከተዘጋ) በኃላ ዘግይተው የሚመጡ መወዳዳሪያ ሰነዶች በግዥ ህግ ተቀባይነትየላቸውም።
13. ማሰልጠኛ ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰርዝ መብት በህግ የተጠበቀ ነው።
14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የማስታወቂያ ሽፋን በቀን 28/12/2017 የወጣ ዕትም ታትሞ ቀርቧዋል። ስለ ጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ሁርሶ ካምፕ ከድሬዳዋ ከተማ 27 ኪ/ሜትር ወጣ ብሎ የሚገኝ ማሰልጠኛ ነው።
በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ሁርሶ ስ/ቁጥር 025 447 0115 በመደወል አስፈላጊ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚ/ር ሠላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት (ሁርሶ)