Your cart is currently empty!
የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ጽ/ቤት ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን /ኮምፒዩተሮችን/ በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ጽ/ቤት ለሺንሽቶ ከተማ አስ/ር ማዘጋጃ ቤ/አገ/ት/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከተመደበላቸው በጀት ላይ ለአገልግሎት ማዘመን ሥራ የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን /ኮምፒዩተሮችን/ በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡–
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ወረቀት ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የቲን ቁጥር ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው
- የጨረታ ማስከበሪያ /በባንክ የተረጋገጠ የብር 10,000 /አሥር ሺህ ብር/ ዋጋ ያለው CPO ማቅረብ የሚችሉ
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ከአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል፤ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ሁለት ኮፒና አንድ ኦሪጅናል ለየብቻ በማሸግ ከአዲስ አበባ በሆሳዕና 295 ኪሎ ሜትር ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ 369 ኪሎ ሜትር በሐዋሳ 137 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከዞኑ ዋና ከተማ ዱራሜ 17 ኪሎ ሜትር በመጓዝ የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን የጨረታ ሠነዱን ከሺንሽቾ ከተማ አስ/ር ገቢዎች ባ/ን/ቅ/ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሺንሽቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-10 በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ሲሆን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተወዳዳሪዎቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዕለቱ 9፡00 የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0463390876/877 ይደውሉ
የሺንሽቾ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት