Your cart is currently empty!
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 01/2017
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1-የፅህፈት መሳሪያ፤
- ሎት 2- የፅዳት ዕቃ፤
- ሎት 3 የመኪና ጌጣጌጥ፤
- ሎት 4 – የቧንቧና የሳኒቴሽን ዕቃዎች፤
- ሎት 5 የኤሌክትሪክ አክሰሰሪ እቃዎች፤
- ሎት 6- የአይሲቲ ዕቃዎች
- ሎት-7 የሞባይል ቀፎ ግዥ
- ሎት-8 የአባላት መታወቂያ ግብዓት ማቅረብና ማሳተም
1. ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1.1 የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
1.2 የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
1.3 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ሰርተፍኬት ያላቸው
1.5 በግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ 9439
1.6 ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ስለግብር አከፋፈል የሚገልጽ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
2. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ 7 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል እንዲሁም በሎት -8 5,000.00 (አምስት ሺ) በመክፍል አራት ኪሎ ፓርላማ ፊት ለፊት በሚገኘው የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-02 በግንባር በመቅረብ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 5 ለእያንዳንዱ ሎት10,000.00 (አስር ሺህ) ብር ለሎት 6 እና 7 ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ለሎት ስምንት (8)5,000,000.00 (አምስት ሚሊየን ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለበት የባንክ ዋስትና ብቻ በብልፅግና ፓርቲ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ከሁለቱ አማራጮች ውጭ የሚቀርብ ማስያዣ ከጨረታ ውጪ ያስደርጋል። ተጫራቾች አሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
4. ተፈላጊውን የጥራት ደረጃ ያልጠበቀ ዕቃ ማቅረብ ከአቅራቢነት ያሰርዛል::
5. ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት በመለየት ዋጋቸውን ጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ብቻ እያንዳንዱ ዋጋ፣ ጠቅላላ ዋጋ እና ቫትን አካቶ ያለውን ድምር በመጨመር ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒውን እንዲሁም ሲ.ፒ.ኦ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ ከ3 ቀናት በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
8. ከጨረታ ሰነዱ ውጪ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
9. ጨረታው በ11ኛው ቀ ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ 1ኛ ፎቅ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
10. የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናል።
11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-124-3459 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት