Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተማሪዎች ማደሪያ ማስፋፊያና ተያያዥ መገልገያዎች እንዲሁም አዲስ ትምህርት ቤት ፕሮጀከት ግንባታ ማስተር ፕላንና ዲዛይን ክለሳ፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር የምክር አገልግሎት የሚሰሩ ደረጃ አንድ የማማከር ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 08, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: – SSNT-T572
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
- ለሎት አንድ ((Lot-1) የተማሪዎች ማደሪያ ማስፋፊያና ተያያዥ መገልገያዎች እንዲሁም
- ለሎት ሁለት (Lot-2) አዲስ ትምህርት ቤት ፕሮጀከት ግንባታ ማስተር ፕላንና ዲዛይን ክለሳ፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር የምክር አገልግሎት የሚሰሩ ደረጃ አንድ የማማከር ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ፕሮጀከቱን የማጠናቀቂያ ጊዜ ስራው ከተጀመረበት በ 365 ቀናት ውስጥ ለሎት አንድ ((Lot -1) እና በ 300 ቀናት ውስጥ ለሎት ሁለት (Lot-2) ይሆናል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፤
- ተጫራቹ ለ2017 ዓ. ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (ገዝ) ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (TIN) ተመዝጋቢ የሆነ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ከሚሰጥ ሕጋዊ አካል ለ2017 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ አንድ ህንፃ ስራ ተቋራጭ የማማከር ፈቃድ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
- የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰላሳ (30) ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E–99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT–T572 በሚል ግቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው (Conditional) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል የጨረታ መክፈቻ ከፍል በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ –
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነኝ ቴክኒካል ክፍል
አቶ አሊ አስፋው
ስልክ ቁጥር፡ 011-517- 4552
ኢ-ሜይል: AliAs@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Ethiopian
የኢትዮጵያ