Your cart is currently empty!
የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት ለንግድ ቤት አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለንግድ ቤት አገልግሎት የሚውል የቤት ኪራይ ለማከራየት
የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ከዚህ በታች በአድራሻቸው የተጠቀሱትን በጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ላይ የሚገኙትን 3 ቤቶችን ማለትም፡–
1. ካራ ቆሬ፡ ኢድራሻ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ወረዳ 03 የቤት/ቁ B/72/06 የቤቱ ስፋት 57.6 ካሬ ሜትር ኮንዶሚኒየም (የጋራ መኖሪያ) ወለል (Ground) ላይ የሚገኝ፣
2. ቦሌ ቡልቡላ፡ አድራሻ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር B/87/01 የቤቱ ስፋት 57.4 ካሬ ሜትር ኮንዶሚኒየም (የጋራ መኖሪያ) ወለል (Ground) ላይ የሚገኝ፣
3. ቦሌ አያት 2፡ አድራሻ ለሚኩራ ክ/ከ/ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር B/55/03 የቤቱ ስፋት 57.76 ካሬ ሜትር ኮንዶሚኒየም (የጋራ መኖሪያ) ወለል (Ground) ላይ የሚገኝ፣ ባሉበት ሁኔታ ለንግድ ቤት አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም የጨረታ መነሻ ዋጋ፡ ለካራ ቆሬ ለአንድ ካሬ 300.00 ብር፣ ለቦሌ ቡልቡላ፡ ለአንድ ካሬ 500.00 ብር፣ ለቦሌ አያት 2፡ ለአንድ ካሬ 400.00 ብር መሆኑን እየገለጽን ማንኛውም ቤቱን በኪራይ ለንግድ አገልግሎት መጠቀምና ማዋል የሚፈልግ ተጫራች።
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የታደሰ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለው፣ ወይም ውል ከተዋዋለ በኋላ የንግድ ፈቃድ አውጥቶ ቤቱን በመከራየትና ለንግድ መጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል (ተጫራቹ የንግድ ፍቃድ የሌለውና ጨረታውን ቢያሸንፍ አዲስ ንግድ ፈቃድ እንደሚያወጣ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት)።
- ተጫራች የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው መሆን አለበት፤
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 306 መግዛት ይችላል።
- ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያውን እና ሌሎች መረጃዎችን የያዘውን የጨረታ ሰነድ በአንድ ላይ በታሸገ ኤንቨሎፕ (አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ) በማድረግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የግዢ ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።
- ተወዳድሮ አሸናፊ የሚሆነው ግለሰብ ድርጅት ተቋሙ በሚያከራየው ቤት ላይ የሚሰራው በህግ የተፈቀዱ ስራዎችን ብቻ ነው።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- አድራሻ፡– ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ኤስኤምኤስኤስ (SMSS) ህንጻ 3ኛ እና 4ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት