Your cart is currently empty!
የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሠራተኛ ደንብ ልብስ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ ባህላዊና ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች እና ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር የካ/መ001/2018
የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የሠራተኛ ደንብ ልብስ
- ሎት 2 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- ሎት 3 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 4 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 5 ቋሚ ባህላዊና ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች
- ሎት 6 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ከላይ ዝርዝራቸው የተጠቀሱትን ዕቃዎችን ለማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- የዘመኑን ግብር የከፈለ
- የቫት ከፋይ የሆነ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይና የቲን ቁጥር የሚያቀርብ
- ሕጋዊ ደረሰኝ (ካሽ ሬጂስተር ደረሰኝ ማቅረብ የምትችሉ
- ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ተጫራቾች የግዢ ጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ / በየሎቱ የበጀቱ 0.5% ወይም ሎት 1/ ብር 7,500 /ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ፣ ሎት 2/ 8,500 /ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ፣ ሎት 3/ 3,370/ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰባ ብር ብቻ፣ ሎት 4/ 7,900 /ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ፣ ሎት 5/ 8,500 /ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ፣ ሎት6/ 7,500 /ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ /ቢድቦንድ / 10 % በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ኦሪጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ አስረኛው የሥራ ቀን ድረስ ማቅረብ አለባቸው፤ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሠዓት ታሽጎ 4፡00 ሠዓት ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም እንዲሁም ከተጠየቀው ስፔስፊኬሽን ውጪ ዕቃ ማቅረብ አይፈቀድም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውና ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም እንዲሁም አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
- በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ከ8ኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ት/ቤቱ ድረስ ገቢ ማድረስ አለባቸው።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡– በተለምዶ አበቤ ሱቅ ፊት ለፊት ያለውን አስፋልት ተሻግሮ እንግሊዝ ኤምባሲ ጎን ባለው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0116-68-60-87/ 0911-83-22-42/0932-89-86-96 መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡– ዋጋው የሚሞላው በወሰዳችሁት የጨረታ ሰነድ ላይ ነው
የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
cttx Art cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Materials cttx, cttx Musical Instruments cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx