Your cart is currently empty!
የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዘመን የተለያዩ ዕቃዎችን በሎት በመክፈል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዘመን ከዚህ በታች የተገለፁ ዕቃዎችን በሎት በመክፈል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- በሎት 02 (ሁለት) ለህግ ታራሚዎች ለትምህርትና ስልጠና የሚውሉ የተለያዩ የብረታ ብረት ስራ ስልጠና ዕቃዎች፤ የእንጨት ስራ ስልጠና ዕቃዎች፤ የኤሌክትሪክ ስራ ስልጠና ዕቃዎች፣ የግንባታ ስራ ስልጠና ዕቃዎች፣ የተለያዩ የቧንቧ ስራ ስልጠና ዕቃዎች ፣ የአውቶ መካኒክ ስራ ስልጠና ዕቃዎች፤ የልብስ ስፌት ስራ ስልጠና ዕቃዎች /ጨርቃ ጨርቅ/፤ የዘመናዊ ሽመና ስራ ስልጠና ዕቃዎች እና የአትክልትና ፍራፍሬ ስራ ስልጠና (የግብርና መገልገያ) ዕቃዎች ሲሆኑ
- በሎት 03 (ሶስት) ለቤቶች እና ለመሰረተ ልማት ዕድሳትና ጥገና የሚውሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች እና የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ናቸው።
- ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ከግዥ ክንውን ቡድን ክፍል በመግዛት በጨረታው ሰነድ ላይ የምትሸጡበትን ዋጋ በመግለፅ በሰም (በሙጫ) በታሸገ ኤንቨሎፕ በመሙላት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የሎት ሁለት ጨረታ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡15 ሰዓት ይከፈታል።
- የሎት ሶስት ጨረታ በ15ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው ቀን 8፡15 ሰዓት ይከፈታል።
- የተገለፀው ቀን ካላንደር የሚዘጋው ሆኖ ከተገኘ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚዘጋ እና የሚከፈት ይሆናል።
- ለመወዳደር የሚመጡ ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 02 (ሁለት) ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት 03 (ሶስት) ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርበታል
- የዘመኑን የመንግስት ግብር ግዴታ መወጣታቸውን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ይኖርበታል (ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች) ማቅረብ
- በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ (WWW.ppa.gov.et) የአቅራቢነት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ናሙና የተጠየቀባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ መሆኑን በማወቅ ዋጋ ተሞልቶ ናሙና አላማቅረብ የተከለከለ ነው።
- ለሚጫረቱት ዕቃ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ከላይ እንደተገለፀው ጨረታው በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 441 4301 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ
ልማት ማረሚ ቤት ማዕከል
cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Food Items and Drinks cttx, cttx Machinery and Equipment cttx, cttx Materials cttx, cttx Products and Services cttx, cttx Raw Materials and Supplies cttx, cttx Water Engineering Machinery and Equipment cttx, cttx Water Pipes and Fittings cttx, Electromechanical and Electronics cttx