Your cart is currently empty!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የድሮን ካሜራ ከነሙሉ አክሰሰሪው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የድሮን ካሜራ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 054/18
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የቀረበውን የድሮን ካሜራ ከነሙሉ አክሰሰሪው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ተ.ቁ |
የዕቃው/አገልግሎቱ ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የሚታሸግበት ሰዓት |
የሚከፈትበት ሰዓት |
ቦታ |
1 |
የድሮን ካሜራ |
በቁጥር |
|
40,000 |
4:00 |
4:30 |
ዲላ ከተማ መምህራን ኮሌጅ ግቢ |
በመሆኑም በንግድ ሥራ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በዲላ ከተማ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ግብርና ቢሮ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነድ በመሙላት የጨረታ የቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ የመጫረቻ ሠነዶችን በአንድ እናት ፖስታ በማዘጋጀት በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት በቢሮው ግዥና/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ተወካዮች/ በተገኙበት ግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ አሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ስምምነት ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20 ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
- የጨረታው ሳጥን መክፈቻ 16ኛው ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 046 131 0134 ይጠቀሙ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ