የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በ2018 በጀት ዓመት ለጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ላፕቶፖች፣ ሞባይል ቀፎ እና ታብሌቶች፣ የጽሕፈት መሣሪያ እና ጋራዥ (የመኪና ጥገና) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በ2018 በጀት ዓመት ለጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ላፕቶፖች፣ ሞባይል ቀፎ እና ታብሌቶች፣ የጽሕፈት መሣሪያ እና ጋራዥ (የመኪና ጥገና) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  • የዘመኑን ግብር የከፈለና አግባብ ያለው የታ ደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው።
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ማንኛውም ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ሙሉ መረጃ የያዘ ሰነድ ከርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ።
  • የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከመ/ቤቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ.2 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው፣ ፈርመው እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድ እና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነዱን ለየብቻ በተለየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፑ የውጪ ገጽ ዋና /ኦሪጅናል ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲሆን ሰነድ የሚያስገቡበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በፊት ብቻ ይሆናል። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋው እና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ የተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የባንክ CPO ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፏቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ እና ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
  • በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 046 1807 970 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የመ/ቤቱ አድራሻ፡- ወላይታ ሶዶ ከሌዊ ሪዞርት ፊት ለፊት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት