የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሠራተኞች የስራ ልብስ የሚሆን የተዘጋጀ የሥራ ልብስ (ጃኬትና ሱሪ) እና ሽርጥ እንዲሁም ጓንት እና መጥረጊያ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 09, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ /የተ/የግል ማህበር ለሠራተኞች የስራ ልብስ የሚሆን

  • ሎት 1የተዘጋጀ የሥራ ልብስ (ጃኬትና ሱሪ) እና ሽርጥ እንዲሁም
  • ሎት 2ጓንት እና መጥረጊያ፣ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት

1. በእያንዳንዱ ሎት ላይ በትከክለኛው የሥራ መስክ የተሠማራና የንግድ ሥራ ፈቃዱን ያሳደሰ

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው

3. የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሎት 1- 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ሎት 2– 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለሁለቱም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ለየብቻው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።

6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።

7. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል ይከፈታል።

8. በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ ወይም ቀንሶ መወዳደር አይቻልም።

9. ማንኛውም ተጫራች ኦሪጅናል የጨረታ ሰነድ ለሁሉም ሎቶች ለየብቻ ኦርጅናል ፖስታ በማዘጋጀት እና በጥንቃቄ ለየብቻ በማሸግ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉንም ሎቶች 1 /በአንድ ፖስታ ማቅረብ አይቻልም።

10. አንድ ተጫራች የንግድ ሥራ መስኩ ከፈቀደለት በሁሉም ሎቶች ወይም የሚፈልገውን ሎት ብቻ መርጦ መወዳደር ይችላል።

11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 16ኛው ቀን ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 400 ላይ ታሽጎ 430 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።

12. የመክፈቻ ቀኑ የሕዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

13. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ሲገለፅለት የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል።

14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት /የጨረታ ሰነድ/ ለየብቻ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

15. አቅራቢ ድርጅቱ የማስጫኛ እና የማስወረጃ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ንብረቱን ለካምፓኒው ንብረት ክፍል ያስረክባል።

16. ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 637 5272 ደውለው ይጠይቁ

የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ /የተ/የግል ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *