Your cart is currently empty!
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ለቨርቹዋል ባንኪንግ የሚሆን ቦታ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Reporter(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ የዕቃ ግዥ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
በዚህም፡–
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/ የአገልግሎት ግዥ
ሎት 1 ለቨርቹዋል ባንኪንግ የሚሆን ቦታ ኪራይ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፤
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፊኬት ያላቸው፤ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሐገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት ለመስጠት ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ፈቃድና የተመዘገቡበት የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ማንኛውም ተጫራች የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽ አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ መሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
6. ጨረታው ከተከፈት በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፤ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።
7. ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳው ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታው የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም እስከ 20% በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዕለቱ ጠዋት 4:30 ይከፈታል።
10. ተጫራቾች በሚጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሻል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document /መሠረት የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ CPO/ ለብቻ እና ፋይናሻል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
11. የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሰነድ ግምገማ ውጤት 40% እና የፋይናንሻል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ቴክኒካል ግምገማ ያላለፈ ተጫራች |ድርጅት ፋይናንሻል እንደማይከፈት እንዲታወቅ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡– ስልክ ቁጥር 011 553 0767/011 515 7337
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት