Your cart is currently empty!
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት የዳቦ መጋገሪያ ማሽን እና የሠራተኞች ጃኬት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ ዕቃ ግዥ /አገልግሎት/ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በዚህም፡– ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/ የአገልግሎት ግዥ
- ሎት 1 የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ግዥ፣
- ሎት 2 ለሠራተኞች ጃኬት ግዥ፣
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው
- ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደስ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ እና ለሎት 2 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲስ ፍል ውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።
- ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሂደቱ የቴክኒከ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ለሎት 1 እስፔስፊኬሽን /Specification/ ግምገማ ውጤት (55%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (45%) ሲሆን ለሎት 2 ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማና የናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (4o%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ነገር ግን ቴክኒካል ግምገማ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ እና ቴክኒካል ናሙና ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል እንደማይከፈት እንዲታወቅ። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዙ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር፡– 0115 53 07 67/011 5 15 73 37
የፍልውሃ አገልገሎት ድርጅት