Your cart is currently empty!
አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Reporter(Sep 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡– ብ/ግ/ጨ-1/2018
አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡–
1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የተእታ ተመዝገቢነት የምስክር ወረቀት እና የታክስ ከፋይ መለያ ቲን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡበት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ ቅደም ተከተል መሰረት ቫትን ጨምሮ ነው።
3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አጠቃላይ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን በአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በሚል ባንክ ጋራንቲ ቦንድ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
4. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ በፍፁም የተከለከለ ነው።
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለያይተው ማቅረብ አለባቸው ይሄ ካልሆነ ያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
6. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ብቁ የሚሆነው በዝርዝር የተቀመጠውን የጨረታ መመሪያ ሲያሟሉና በጨረታ መመሪያ መሰረት ሲያቀርብ ነው የጨረታ መመሪያ ያላሟላ ተጫራች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።
7. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉበትን እቃዎች ከእስቶራቸው ወዲያውን ማቅረብ እንደሚችሉ በመወዳደሪያ ሰነዳቸው ላይ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።
8. የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት 1500.00 (አንድ ሺ አምሰት መቶ ብር) አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በሚል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000606340692 በማስገባት ኦሪጂናል ደረሰኝ ብቻ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መከላከያ መኮንኖች ክበብ የቢሮ ቁጥር 308 መውሰድና ማየት ይችላሉ።
9. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን አየር ላይ ውሎ በ15ኛው ቀን በ7፡30 ሰዓት ታሽጎ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል ዕለቱ ሰንበት ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
10.አድራሻ ቦታ መከላከያ ስራዊት መኮንኖች ክበብ ቢሮ ቁጥር 308 ሲሆን ስልክ ቁጥር:- 011-384-4111
11.አክሲዮን ማህበሩ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ