Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉርድ ሾላ አካባቢ ሊያስገነባ ላቀደው 2G+G+12 ሕንፃ የጂኦቴክኒካል ጥናት /የአፈር ምርመራ/ ስራ ለመስራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Reporter(Sep 17, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉርድ ሾላ አካባቢ ሊያስገነባ ላቀደው 2G+G+12 ሕንፃ የጂኦቴክኒካል ጥናት /የአፈር ምርመራ/ ስራ ለመስራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡–
1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን (Specification) መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፤
6. ፌዴሬሸኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
ለበለጠ መረጃ፡– 011 647-9794/ 011 647-9578 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ. ፋክስ 011 645-0879 ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን