Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ.የተ. የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እና የስትራቴጂ ልማት ጥናት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ.የተ. የሥርዓተ–ፆታ እኩልነት እና የስትራቴጂ ልማት ጥናት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ.የተ. ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች በዚህ የሥራ ዘርፍ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ቲን፤ ቫት፣ የንግድ መዝገባ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ90 ቀን ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ፣ ሲፒኦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የዋጋውን 10% (አስር ፐርሰት) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
4. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ እና አገልግሎት የሚሰጡበትን ዋጋ የያዘ ፋይናንሽያል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ22ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በዚሁ እለት 4፡00 የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚህ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
5. የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡– አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12
ስልክ ቁጥር :- 0910645442
የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ