የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የስንዴ ምርት ግዥ በጨረታ በማወዳደር ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ ንሥኮ/ብግጨ 01/2018

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የስንዴ ምርት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በጨረታ በማወዳደር ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።

1. የስንዴ ምርት ግዥ አጠቃላይ ብዛት 500 ሺህ ኩንታል

  • የሚፈለገው የጥራት ደረጃ፣
  • የምርት ዘመን 2016/2017
  • የእርጥበት ልክ ከ13% ያልበለጠ፤
  • የባእድ ስሪት መጠን 2% ያልበለጠ፤
  • የቀጨጨ፣ የተሰባበረ፣ መልኩን የቀየረ በብርድ የተመታ 6% ያልበለጠ፤
  • ጠቅላላ የጥራት ጉድለት 8% ያልበለጠ፤
  • ከእርጎነትና እስመት ነፃ የሆነ፤
  • ሕይወት ካለው ተባይ ነፃ የሆነ፤

የማቅረቢያ ቦታ፡አዲስ አበባ፣ አዳማ እና ድሬዳዋ በኮርፖሬሽኑ መጋዘኖች

2. ተጫራቾች በዘርፉ 2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስከር ወረቀት፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ከሊራንስ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ስርተፊኬት /TI/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፐሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ከመስከረም 7 ቀን 2018 . ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ 200 600 ሰዓትንዲሁም ከሰዓት 700- 1100 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ 200-630 ሰዓት ድረስ ማዕከል ግዥ ዋና ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ መስከረም 22 ቀን 2018 . 430 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በሲፒኦ፣ ጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

7. የቴከኒከ ሰነድ እና የፋይናንሻል ሰነድ በፖስታ በማሸግና ኮፒ እና ኦሪጅናል የፋይናንሻል እንዲሁም የቴክኒካል ሰነድ ኮፒዎችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ሁሉንም ፖስታዎች በማድረግ መስከረም 22 ቀን 2018 . 430 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋናው መቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። አድራሻ ከታች ተገልጿል።

8. ተጫራቾች የስንዴ መሸጫ ዋጋ 3 ማቅረቢያ ቦታዎች ለየብቻ ተለያይቶ ዋጋ ማቅረብ አለባለቸው።

9. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን ለአሸነፉበት የስንዴ ምርት ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል።

10. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 011-418-7345/ 011-466 9336 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡ደብረዘይት በሚወስደው መንገድ በቅሎ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *