Your cart is currently empty!
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የRDF መድኃኒትና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ጊዜየወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡- GGWW/0001/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በRDF በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኝ ለግብርና ሴክተር የሚሆን የRDF መድኃኒትና ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ለግዢ የቀረቡ እቃዎችና የጨረታ ማስከበሪያ CPO
- ሎት አንድ፡ የRDF መድኃኒትና ዕቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ብር
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች፡-
- የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፤ የቫትና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦላይን /online/ ሲስተም የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት የጨረታ ሰነዱ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ዶክመንት ሲያቀርቡ ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ ከቴክኒካል ኦሪጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም ሁሉንም በአንድ አናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት፡፡
- የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል። ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ደግሞ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
1. በግዢ ኤጀንሲ በዕቃ አቅርቦት ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርቶችም መወዳደር አይችሉም፡፡
2. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው እቃዎች የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ተመላሽ ይሆናሉ፡፡
3. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸውን ማንኛውም እቃ የወረዳው ማዕከል ማለትም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሀል አምባ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የወረዳው ማእከል ርቀት ከአዲስ አበባ 116 ኪ.ሜ ነው፡፡
4. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 011-336 0631/ 011–336-0148
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት