የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን የኦዲት ባለሙያዎችን ወደ ተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች አሰማርቶ ሊሰራ ላቀደው የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ጠንካራ የመስከ መኪና ማቅረብ የሚችሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ሊከራይ ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

/ቤታችን የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን የኦዲት ባለሙያዎችን ወደ ተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች አሰማርቶ ሊሰራ ላቀደው የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ጠንካራ የመስከ መኪና ማቅረብ የሚችሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ሊከራይ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች በተገለፀው ዝርዝር መሰረት የኮርፖሬሽናችንን ኦዲተሮች በመያዝ በየክልሉ ከተሞችና ወረዳዎች የሚሰማሩና በተሰማሩበት መስክ አስፈላጊውን አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ፣

  • ስሪታቸው እኤአ 2020 በኋላ 4 Wheel Drive የሆኑ በሊትር 8 ኪሎ ሜትር እና ከዚያ በላይ መጓዝ የሚችል ጠንካራ፣ ብልሽት የሌለባቸውና ለስራው ምቹ የሆኑ፣
  • በሁሉም ክልሎች የመስክ መኪና ከአሽከርካሪው ጋር 3 ለሶስት/ ወር ከመስከረም 24/2018 . እስከ ታህሳስ 24/2018 . ድረስ በመስክ ስራ ላይ የሚቆዩ፣
  • የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 710 በመቅረብ በኮርፖሬሽኑ የስራ ቀንና ሰዓት (ቅዳሜና እሁድን) ሳይጨምር ጠዋት 230 እስከ 630 ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት እስከ 1100 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
  • ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ10 (አስር) የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 500 ላይ ይከፈታል
  • ዕለቱ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  • ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመቀበል ሆነ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፦

  • ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተገለጹትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፣
  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
  • ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
  • ሶስተኛ ወገን የመድን ዋስትና፣
  • ሊብሬ
  • የቴከኒክ ምርመራ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ለመሳተፍ ከላይ የተመለከቱትንና ሌሎች ማስረጃዎች በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) Audit Service Corporation ስም በሲፒኦ ብቻ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል።
  • አድራሻ፡የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን (Audit Service Corporation)

የስልክ ቁጥር 0115547615

የፖስታ . 5720

ካዛንችስ ከሲንቄ ባንክ ፊትለፊት

የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *