Your cart is currently empty!
ሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ የመስክ አገልግሎት መኪናዎችን ለአንድ ዓመት ጊዜ በቁርጥ ዋጋ መከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመስክ መኪና አከራዮች ምዝገባና ለመኪናዎች አቅርቦት የወጣ ማስታወቂያ
ሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ አከራዮችን መዝግቦ ከዚህ በታች በተገለጸው ዝርዝር መሰረት አነስተኛ የመስክ አገልግሎት መኪናዎችን ለአንድ ዓመት ጊዜ በቁርጥ ዋጋ መከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ ውል ገብተው መኪና እያቀረቡ ያሉትና ሌሎች ማከራየት የሚፈልጉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቀርቦ መመዝገብና ውል ገብቶ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እሳወቅን
ተመዝጋቢዎችም፡-
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የቫት ምዝገባና የቲን ሴርትፊኬት ማቅረብ የሚችሉና፣
2. ከአንድ መኪና ጀምሮ መኪኖችን ማቅረብ የሚችሉና ቢያንስ የአንድ መኪና የባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ውክልና ማቅረብ የምችሉ መሆን እንደሚኖርባቸው እንገልጻለን።
የአቅርቦቱ ዝርዝር እንደሚከተስው ይሆናል፡–
ተ.ቁ |
የመኪና ዓይነት |
የሥሪት ዘመን |
የአንድ ቀን ዋጋ ቫት ጨምሮ ያለነዳጅ (በብር) |
የሚቀርበው ብዛት
|
ውሉ የሚያበቃበት ጊዜ
|
1 |
ባለአንድ ጋቢና ፒክ አፕ ወይም ኪንክ ካፕ |
እ.ኤ.አ. ከ1995 ጀምሮ |
1,890
|
ከአንድ ጀምሮ እንደስፈላጊነቱ እየታዘዘ የሚቀርብ |
ለአንድ ዓመት ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ የሚታደስ |
2 |
ባለሁለት ጋቢና ፒክ አፕ |
1,990 |
|||
3 |
ሽፍን(ሽቴሽንዋገን) |
2,500 |
መመዝገቢያ አድራሻ፡– በሲደማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት አከባቢ የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጄንሲ ባለበት ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ስልክ፡– የቢሮ 046 212 4700፣ ሞባይል 09 16 03 55 92/ 09 08 28 06-1
ሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ