በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሆነ የደህንነት ካሜራ ግዥ እና ገጠማ፣ የጊቢ ውበት በተለያዩ አበባዎችና አትክልቶች ማስዋብ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራትና ለመግዛት ይፈልጋል


Yedebub Nigat(Sep 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሥራዎችንና የዕቃ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራትና ለመግዛት ይፈልጋል።

1ኛ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሆነ የደህንነት ካሜራ ግዥ እና ገጠማ ለማድረግ ይፈልጋል።

2 የጊቢ ውበት በተለያዩ አበባዎችና አትክልቶች ማስዋብ

ስለዚህ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅድመ መሥፈርቶች እንደሚከተሉት ናቸው፡

1) በዘርፉ የተፈቀደና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ድጋፍ ማቅረብ የሚችል

2) የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒዮ ማቅረብ የሚችል

3) ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሠነድ ላይ ብቻ በግልጽ በማሙላት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድነት አድርጎ በሁለት ኮፒ እና አንድ ኦርጅናል በተለያዩ ሶስት (3) ፖስታ በማድረግ ሁሉንም በሰም በታሸገ ኢምፕሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 15 ቀን 2018 / ድረስ በተከታታይ የስራ ቀናት ጠዋትና ከሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ እየገለጽን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 16 ቀን 2018 / ከጠዋቱ 400ሰዓት ላይ ይከፈታል።

4) አሠሪው / ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

5) ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ገበያ ዋጋ በታች ያቀረበ እንደሆነ አሰሪው /ቤት ውል ለመግባት አይገደድም።

  • በእጅ የተሞሉ ሠነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል።
  • አዲሱ የተሻሻለው የደቡብ ኢት/ ክልል መንግስት ግዥ መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል።
  • የጨረታ ዝርዝር ሃሳብ ከጨረታ ሠነዱ ግዥ ላይ ማግኘት ይችላል።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0926265338/091325086/0910658153

የሶዶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ /ቤት