Your cart is currently empty!
አዋሽ ባንክ አ.ማ አክሲዮኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 21, 2025)
Addis Zemen(Sep 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የአክሲዮን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ባንክ አ.ማ የተሻሻለው የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 ከመውጣቱ በፊት የውጭ ዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን የሚከተሉትን አክሲዮኖች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ምድብ /ሎት |
ለጨረታ የቀረቡ አክሲዮኖች ሰርተፍኬት ቁጥር |
የአክሲዮኖቹ ብዛት |
የአንዱ አክሲዮን መነሻ ዋጋ |
የአክሲዩኖቹ ጠቅላላ መነሻ ዋጋ |
1 |
44030 እና 54402 |
178 |
1,000.00 |
178,000.00 |
2 |
06751 እና 02660 |
3 |
1,000.00 |
3,000.00 |
በመሆኑም፡–
1. የኢትዮጵያ ዜጋ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/73/20 ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የውጭ ዜጎች እና ድርጅቶች በጨረታው በመሳተፍ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከጨረታው ቀን በፊት ከባንኩ የባለአክሲዮኖች አካውንትስ ዋና ክፍል ብር 200 (ሁለት መቶ) ከፍለው በመውሰድ ቅጹን ሞልተው በኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ከባንኩ ዋና መ/ቤት ጀርባ ባንኩ በተከራየው ኢያሜክስ ህንፃ የመሬት ወለል ላይ ባለው የባለአክሲዮኖች አካውንትስ ዋና ክፍል ማስገባት አለባቸው።
3. ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት ቦታ ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን አክሲዮኖቹን ተጫርተው የሚገዙበትን ዋጋ 25% (ሀያ አምስት በመቶ) በአዋሽ ባንክ ስም በተሠራ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች በቀረበ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
6. በአንድ ሎት (ምድብ) የቀረቡ አክሲዮኖችን ከፋፍሎ ዋጋ ማቅረብ/መጫረት አይቻልም።
7. ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች ደግሞ ቢጫ (የሎው) ካርድ እና ፓስፖርት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
8. ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው በውጭ ምንዛሪ ብቻ ሲሆን ጨረታውን ካሸነፉም ክፍያ መፈፀም የሚቻለው ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሪ ብቻ ነው።
9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
10. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአምስት /5/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
11. ተለያይተው የቀረቡትን ሎቶች (ምድቦች) መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ምድብ (ሎት) በተለያየ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስያዣ ሲፒኦውም ተለያይቶ መቅረብ አለበት።
12. በሌሎች ሕጎችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጎች ተፈፃሚነት አላቸው።
13. ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ 0115-57-00-92/0115 571 823
ፖ.ሳ.ቁ 12638
አዋሽ ባንክ አ.ማ