Your cart is currently empty!
የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ 103ኛ ኮር ጠ/መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አይነት የህሙማን ማገገሚያ ቀለብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ 103ኛ ኮር ጠ/መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አይነት የህሙማን ማገገሚያ ቀለብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣ የቫት ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸውን ይጋብዛል።
ተጫራቾቹ የጨረታውን ዝርዝር መምሪያና ዝርዝር ሰነድ የያዘ 200.00 /ሁለት መቶ / ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ግምቢ የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳደር ግቢ የሚገኘው የ103ኛ ኮር ፋይናንስ ቢሮ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት በቢሮው ወደተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው መስከረም 27 ቀን 2018ዓ.ም ከሰዓት 8:30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ ቁጥር፡– 0919 079 321 / 0917 934 023
በማዕከላዊ ዕዝ ጠ/መምሪያ የ103ኛ ኮር መምሪያ